አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ

ኡሞድ ኡጁሉ ኡቡፕ

ሚኒስትር ደኤታ

አቶ ኦሞድ ኦጁሉ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) ፍትህ ሚኒስቴር የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በዚህም ኃላፊነታቸው ለሚኒስቴሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትን ማለትም፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎትን፣ የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽንን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን እና የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽንን ያስተባብራሉ።

አሁን ካሉበት ሹመት በፊት አቶ ኦሞድ ኦጁሉ ለ31 ዓመታት ያህል በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። የቀድሞ ኃላፊነቶቻቸውም የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣ የጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሁም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነትን ይጨምራሉ።

የትምህርት ዳራ

  • የህግ ድግሪ (ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ)
  • ማስተር ዲግሪ (ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨሲቲ ፣ በንጽጽረ መንግስታዊ ህግና መልካም አስትዳደር)

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

News From Advisor State Minister