በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና በታላቋ ሶሻሊስትና ሕዝባዊ ሊቢያ አረብ ጀማህሪያ መካከል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና የሁለትዮሽ ጥበቃ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ጥር 18 ቀን 1996 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፤
ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋይ ሀገሮች ሕጎች መሠረት ስምምነቱ መጽደቁን የሚያረጋግጡ ሰነዶች በዲፕሎማቲክ አካላት አማካኝነት ልውውጥ ከተደረገ በኋላ እንደሆነ በስምምነቱ በመገለፁ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 8 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•