ለገጠር ከተሞች ኤሌክትሪክ ሥርጭት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 9 ሚሊዮን 350ሺ የአሜሪካን ዶላር (ዘጠኝ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃምሣ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት መካከል እ.ኤአ. ሜይ 3 ቀን 2001 በካይሮ የተፈረመ በመሆኑ፤
መሠረታዊ የኢኮኖሚ አለም አቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 28 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•