የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥትንና ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርገው የወጡ ሕጎችን፣ ሐገሪቱ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው የእስረኛ አያያዝ ደረጃዎችን ባከበረ ሁኔታ በፍርድ ቤቶች የሚሰጡ ውሳኔዎችን ማስፈፀም በሚያስችል ሁኔታ ማደራጀት በማስፈለጉ፤
ማረሚያ ቤቶች የእስረኞችን ሰብአዊ ክብርና መብት በማክበር እንዲሁም የእስረኞቹ ግላዊ ሁኔታ በሚጠይቀው የፍርድ አፈፃፀምና እርማት ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግና ከሕብረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበትን ሥርዓት መደንገግ በማስፈለጉ፤
እስረኞች ባላቸው የአደገኛነት ባህሪ ወይም ባላቸው የጉዳት ተጋላጭነት ወይም በፆታቸው እንዲሁም ከፍርድ በፊት በማረፊያ ቤቶች የሚቆዩ እስረኞች ሊደረግላቸው የሚገባውን አያያዝ መደንገግ በማስፈለጉ፤
ማረሚያ ቤቶች ለእስረኞች እንዲሁም ለመላው ሕብረተሰብ በእኩልነትና በፍትሐዊነት የተቀላጠፈ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉበትን ሕጋዊ ማዕቀፍ መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•