በአገልግሎት ላይ

የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ

በሀገራችን ግለሰቦች በግል ዳታቸው ላይ ያላቸውን መብት በዝርዝር የሚደነግግ ሕግ ባለመኖሩና የግል ዳታ ጥበቃ ተቆጣጣሪ ተቋም አለመሰየሙ ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ሥርዓት እንዳይፈጠር የራሱን አሉታዊ ድርሻ ያበረከተ በመሆኑና ዳታ በሚሰበሰብበትና በሚቀናበርበት ወቅት የግል ዳታ ጥሰት እንዳይፈጠር ለመቆጣጠር የሚያስችል የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤

የዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገትን ተከትሎ በመረጃ መረብ አማካኝነት በቀጥታ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዓይነት እና ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን አገልግሎቶቹ የተጠቃሚውን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ እና የተሳለጡ እንዲሆኑ የግል ዳታዎችን መሰብሰብ አስፈላጊ በመሆኑና በዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የተሰባሰቡ የግል ዳታዎችን ማቀናበር ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለው ሚና እያደገ በመምጣቱ፤

ከግል ዳታ ጋር የተያያዙ የመብት ጥሰቶች ሲከሰቱ ውጤታማ መፍትሄዎችን ለመስጠት፣ ከዳታ ማቀናበር ሥራዎች ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመቀነስ፣ ፈጠራን ለማበረታታት፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ እምነት ለመፍጠር እና ኃላፊነት የሚሰማው የዳታ ማቀናበር ባህልን ማሳደግ ወሳኝነት ያለው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ የግል ዳታ ጥበቃ ሥርዓት ዓለም አቀፋዊ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ በመገንባት የግል ዳታ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጪ ሀገር፣ እንደዚሁም ከሀገር ውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በማዘዋወር የሚገኙ መልካም ዕድሎችን መጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1321 /2016
ቀን: ሐምሌ 17፥ 2016 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

1346/2017

ጥር 5፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ