በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት የዳኝነት ሥልጣን በፌደራል እና በክልሎች ፍርድ ቤቶች በመሆኑ፤
ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት የማቅረብና ዉሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለዉ መሆኑ፤በህገ መንግስቱ የተደነገገ በመሆኑ፤
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለሕግ የበላይነት፣ ለሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የበኩላቸውን የማይተካ ሚና የሚወጡበትን ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሕገ-መንግስቱ ስለዳኝነት ነፃነት በተደነገገዉ መሠረት ተግባራቸውን ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ውጤታማ ፣ ቀልጣፋ ፣ ተደራሽ እና ተገማች የሆነ አገልግሎት መስጠታቸው አስፈላጊ በመሆኑ፤
የዳኝነት ሥርዓቱን ለማጠናከር የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በበጀት ምደባና አስተዳደር፣በሰው ሀብት ቅጥርና ምደባ እንዲሁም አስተዳደር ራሳቸውን ችለው የሚሰሩበትን የሕግ ማዕቀፍ እና የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1986 በተደጋጋሚ መሻሻሉ ለአሰራር አመቺ ባለመሆኑና በተሻሻለ አዋጅ መተካት ስላስፈለገ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀፅ (1) መሠረት የሚከተለው ታውጃል፡፡
•
•
•
•
•
•
•