በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ ግዴታ የሚጥሉ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የተረጋገጠውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትና ለዜጎች የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ከማኅበራዊ፡ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና ከቴክኖሎጂ እድገት ጋር የሚጣጣም ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤
ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የመገናኛ ብዙሃን መብቶች በሕገ- መንግሥቱ የተረጋገጡ ሌሎች ሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነቶችን ለማረጋገጥ ያላቸውን ፋይዳ በመገንዘብ እና በሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ስኬታማ እንዲሆን መገናኛ ብዙሃን የሚጫወቱትን የማይተካ ሚና በመረዳት ይህን ሁኔታ ሊያስተናግድ የሚችል ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤
ጥራቱን የጠበቀና ተደራሽ የሆነ የመገናኛ ብዙሃን አሰራር እንዲስፋፋ ማድረግ ለፈጣንና ቀጣይነት ላለው ሁለንተናዊ ዕድገት ቁልፍ የሆነውን በመረጃ የበለፀገ ህብረተሰብ ለመፍጠር የሚያስችልና ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን በማመን፤
መገናኛ ብዙሃን የሕዝብን ሠላምና ደህንነት እንዲሁም ተነፃፃሪ መብቶችና ጥቅሞችን ባከበረ መልኩ በኃላፊነት መንቀሳቀሳቸውን ማረጋገጥና በሕግ መሠረት እንዲሠሩ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍና ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው መንግሥት ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•