በኢትዮጵያ እና በጆርዳን መካከል የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በማስፈለጉ፤
በጆርዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው እና መብትና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በአገራቱ ፍላጎት ያለ በመሆኑ፣
ይህንን የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እ.ኤ.አ. ጁላይ 12 ቀን 2003 የፈረመው በመሆኑ፤
ይህን ስምምነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም በአካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•