የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 27 (2) በዜጎች የሃይማኖት አስተዳደር ተቋማት የማቋቋም መብት በመጠቀም የኢትዮጵያ የወንጌሳዊያን አብያተ-ክርስቲያናትና የአብያተክርስቲያናት ህብረቶች ያቋቋሙትን ሀገር አቀፍ ተቋም የህግ ሰውነት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ-ክርስቲያናት ካውንስል በርካታ የህዝብ ቁጥር ያለውን የወንጌል አማኞች ማህበረሰብ በመንግስት ዘንድ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወክል ተቋም ስለሆነ ህጋዊ ሰውነትና እውቅና በአዋጅ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•