የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሴት አመራሮችን የለውጥ አመራርነት ክህሎት ማሳደግ እንደሚገባ ተመላከተ

It Was Indicated That Strengthening Women Leaders' Transformational Leadership Skills Is Essential to Ensure Gender Equality

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶች፤ ሕፃናት እና ባለ ብዙዘርፍ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ከUN-Women እና የአፍሪካ አመራርነት ልህቀት አካዳሚ (AFLEX) ጋር በመተባበር “የለውጥ አመራርነት ለሥርዓተ-ጾታ እኩልነት” በሚል ርዕሰ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለተቋሙ እንዲሁም ለተጠሪ ተቋማት ሴት አመራሮች ሰጠ፡፡

በተባበሩት መንግስታት የUN-Women የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ሻድራክ በመድረኩ እንደተናገሩት በቂ የሆነ ክህሎት ያላቸው ሴት አመራሮችን ማፍራት የሥርዓተ-ጾታ እኩልነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የማይተካ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፤ በተለይ በፍትሕ ዘርፉ ውስጥ የለውጥ አመራርነት ክህሎት ያላቸው ሴቶች መኖራቸው በህገ-መንግስቱ እና በተለያዩ ኮንቬንሽኖች ለሴቶች የተሰጡ መብቶችን ለማስጠበቅ እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃን በበኩላቸው የሴቶችን የአመራርነት ክህሎት ከማሳደግ አኳያ የለውጥ አመራርነት ክህሎት ትልቁን ሚና እንደሚጫወት ገልፀው፤ ፍትሕ ሚኒስቴር ሴቶችን ከማብቃት እና ለጉዳዩ ትኩረት ከመስጠት አንፃር ሊተገበር የሚገባ ስለሆነ መስል ጉዳዮች ላይም በቀጣይ ተቋሙ በስፋት የሚሰራበት ይሆናል ብለዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶች ሕፃናት እና ባለዘርፍ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ወ/ሮ ዳግማዊት አላምኔ ሥልጠናው በተለይ የአመራርነት መሰረታውያን፤ ኮሙኒኬሽን እና ግጭትን ማስተዳደር፤ራስን ማብቃት፤ ሥርዓተ-ጾታ እና አመራርነት በሚሉ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ነጥቦችን ያካተተ እንደሆነ ገልፀል፡፡

በሥልጠናው ላይ ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የተወጣጡ 80 ሴት አመራሮች የተሳተፉበት ሲሆን፣ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአፍሪካ አመራርነት ልህቀት አካዳሚ እንደተካሄደ ተገልፁዋል፡፡

Tagged Under: Capacity Building civil liberties communication skills conflict management development Equality Ethiopian Ministry of Justice gender Gender Equality gender mainstreaming Justice Leadership leadership skills development legal empowerment ministry program Rule of Law skills Training training program un women women women empowerment women's Women's Rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች