የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የባለሙያዎች የነቃ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

Active Participation of Experts Emphasized for Ensuring Gender Equality

በፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶች ሕፃናትና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት በስርዓተ ጾታ አካቶ ትግበራ ዙሪያ ለተቋሙ የአስተዳደር ሰራተኞች በሁለት ዙር በቢሾፍቱ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተጠናቋል።

የሴቶች ሕፃናትና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት አላምኔ እንዳሉት የሥልጠናው ዓላማ በፍትሕ ዘርፍ የሴቶችን ፤ሕፃናትን ፤ወጣቶችን ፤አካል ጉዳቶችንና አረጋዊያንን አካቶ ለመተግበር እና የተሳትፎ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በአካቶ ትግበራ ዙሪያ ለተቋሙ አስተዳደር ሰራተኖች ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም የስራ ክፍሉ የሴቶችና ህጻናት እንዲሁም ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ተካተው መተግበራቸውን የመከታተል ዋነኛ ኃላፊነት የተሰጠው መሆኑን አንስተው፣ ሥልጠናው የተቋሙ ሰራተኞች አካቶ ከመተግበር አንፃር እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን መነሻ በማድረግ የኦዲት ጥናት ተካሂዶ በጥናቱ ግኝት መነሻነት የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሥልጠናው የአካቶ ትግበራ ምንነት እና ዋና ዋና ጉዳዮች፤ የማካተት አስፈላጊነት የማካተት ስልቶች፤ የማካተት ደረጃ ፤ለአካቶ ትግበራ ምላሽ ሰጪ ተቋማት ባህሪያት የስርዓተ ጾታ ዋና ዋና ጉዳዮች እና የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፎች የሚሉት ተዳሰውበታል ፡፡

ሥልጠናውን ተከትሎ በተሳታፊዎች ለቀረቡ ሀሳብ አሰተያየቶች በአሰልጣኞች አማካኝነት ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የግንዛቤ ማስጨበጫ የሥልጠና መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: bishoftu building capacity Capacity Building children's Children's Rights disability disability rights elderly rights Equality gender Gender Equality gender equity gender mainstreaming governance inclusive inclusive governance legal framework mainstreaming participatory development program Rights Stakeholder Engagement Training training program women's Women's Rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች