የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት

ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ማዘጋጀትና ሪፖርት ማቅረብ፣ እንደ አስፈላጊነቱ መደበኛ በሆኑ ሕግጋት እና የአሠራር ሥርዓቶች መሠረት በማድረግ የሰብዓዊ መብት መከበርን የሚያረጋግጡ ተግባራት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በጋራ መሥራት፣ በመርሐ-ግብሩ ዙሪያ ለፈፃሚ ተቋማት፣ ለኅብረተሰቡና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ መፍጠር፣ በመርሐ-ግብሩ እንዲከናወኑ የተቀመጡ ተግባራት ፈጻሚ አካላት ተብለው በተለዩት የፌዴራል ተቋማት፣ የክልል እና ከተማ መስተዳደር ተቋማት ዕቅዶች ውስጥ ማካተታቸውን ማረጋጥ፣ በዓመት አንድ ጊዜ በድርጊት መርሀ-ግብሩ የተካተቱትን የሰብዓዊ መብቶች አስመልክቶ አገር ዓቀፍ የአካል ክትትል በማድረግ አጠናቅሮ ለብሔራዊ አስተባባሪ ቦርድ ማቅረብ፣ በፖሊስ ጣቢያ እና መምሪያዎች እንዲሁም በፌዴራል እና በክልል ማረሚያ ቤት የተያዙ፣ የታሰሩ እና የተፈረደባቸውን ሰዎች በመደበኛነት ወይም በድንገት መጎብኘት፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ መሠረት መፈጸሙን ማረጋገጥ፣ ሕገ ወጥ ተግባር እንዲታረም ማድረግ እንዲሁም ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሠረት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጥቆማ ወይም አቤቱታ መሠረት በማድረግ የቅድመ ምርመራ ሥራ መሥራት፤ በቅድመ ምርመራ ሥራው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን ሲያረጋግጥ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣ የእርምት እርምጃውን ሂደት መከላከል፣ ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸውን ዓለም ዓቀፍ እና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች አፈጻጸማችን የመከታተል፤ ለሚነሱ ጉዳዮች እንደ አግባብነታቸው ምላሽ የመስጠት እንዲሁም የስምምነቶቹን ብሔራዊ የአፈጻጸም ሪፖርት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን ማዘጋጀት፣ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ እና የመረጃ ማስጨበጫ ሥራ መሥራት እና ሪፖርቶችን ማጠናቀር፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን በጊዜያዊነት ማስተባበር ከተሰጡት ዋና ዋና ኃላፊነቶች መካከል ናቸው፡፡

    የሥራ ክፍሉን ያግኙ

    የሥራ ክፍሉ መሪ

    አወል ሱልጣን መሃመድ

    ዳይሬክተር

    News From Directorate for National Human Rights Monitoring