የንግድ እና ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ-ግብር የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ በኦሮምያ ክልል ተካሄደ

The Ministry Gathers Input in Oromia for New Business and Human Rights Action Plan

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ዳሬክቶሬት ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ሌሎች አጋር አካላት በመሆን ያዘጋጁትና በንግድ እና ሰብዓዊ መብት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የግብዓት የማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዱዋል፡፡

በአባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች ምርቃት በተጀመረው በዚህ መድረክ ፤ የጨፌ ኦሮምያ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ፤ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፤ የንግዱ ማሕበረሰብ፤ ሲቪል ማህበራት፤ የአገር ሽማግሌዎች፤ የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት የተወከሉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

መድረኩ በዋናነት ለዜጎች መብት ቅድሚያ መስጠት ስለሚያስችለው የንግድና ሰብዓዊ መብት ምንነትን ግንዛቤ የመስጠት በሌላ በኩል እስካሁን በነበሩ መድረኮች ላይ ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የተሰባሰቡ ግብዓቶችን ምሉዕ አድርጎ ተቀባይነት ያለው ብሄራዊ የድርጊት መርሃ-ግብር ለማዘጋጀት በኦሮምያ ክልል በኩል ያለውን ሀሳብ በተወካዮቹ አማካኝነት መቀበልን አላማ ያደረገ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

መንግሥት የዜጎችን የኢኮኖሚ፤ ሲቪል፤ ፖለቲካና የባሕል መብቶች በማናቸውም ሁኔታ እንዳይሸራረፉ እና እንዲጠበቁ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ ሲሆን፤ በተጓዳኝ የንግድ ተቋማትም ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የሠራተኞቻቸውን መብቶች ማክበር የሚጠበቅባቸው እንደሆነ ተወስቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ለንግድና ሰብዓዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መስፈርቶችን አዘጋጅቶና በተለያዩ አገራት የድርጊት መርሃ-ግብር እያዘጋጁ ተግባራዊ ማድረግ መጀመራቸው እንዲሁም ደግሞ መንግስት የተቀበልናቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የማክበር ግዴታ ስላለበት ብሄራዊ የንግድና ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብር እንዲዘጋጅ ቁርጠኛ የሆነ አቋም መያዙ ተጠቅሷል፡፡በዚህ መሰረት፤ እንደ አገር የሚኖሩ አሉታዊ ተዕጽኖዎችን ለማስቀረት፣ የንግድ ተቋማት ከሰብዓዊ መብት መከበር ጋር ተያይዞ የሚኖራቸውን ኃላፊነቶች ለማሳወቅና ተጎጂዎችን የመካስ ስርዓትን ለመፍጠር የሚረዳ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መስፈርቶች የሚያሟላ፣ ግልጽና አሳታፊ፣ አውድ ተኮር እና ሊከለስ የሚችል የድርጊት-መርሃ ግብር የማዘጋጀት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ ንግድና ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የሚልና የሰብዓዊ መብት ጽንሰ ሐሳብ፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት መርሆችና መመሪያዎች፤ እንዲሁም ብሄራዊ የንግድና ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት የተከናወኑ ምልከታዎችና የተገኙ ግብረ መልሶችንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን የሚያብራራ ሰነድ በቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ ተሳታፊዎች በተለያዩ የቡድን አደረጃጀቶች በመከፋፈል ለውይይት መነሻ እንዲሆኑ ተደርገው በተዘካጁ ጥያቄዎች ላይ ውይይት በማድረግ ለግብዓት የሚሆኑ ሃሳብ አስተያየቶችን አንስተዋል።

ተመሳሳይ የግብዓት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረኮች በተቀሩት ክልሎች እደሚካሄዱ ታውቋል፡፡

Tagged Under: act action Action Plan african charter on human and peoples’ rights african charter on the rights and welfare of the child african commission on human and peoples' rights bus business Business and Human Rights commerce Convention on the Rights of the Child decree human Human Rights input law legislation ministry national human rights action plan new oromia plan Policy proclamation Regulation right Rights statute Trade un guiding principles on business and human rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች