በታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

Training Provided on the Human Rights Treatment of Detainees and Suspects

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ ሰብዓዊ መብቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ከዴንማርክ የሰብዓዊ መብቶች ኢንስትቲዩት በመተባበር ለድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እና ፖሊስ ኮሚሽን የስራ ሀላፊዎች እና አባላት በታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ ሰብዓዊ መብቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን በሥልጠና መድረኮቹ እንደተናገሩት፣ የሥልጠናው ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ፖሊስ በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ዙሪያ የተሻለ እውቀት እና ግንዛቤን ጨብጦ በስራ ላይ መሠረታዊ ለውጥ በማምጣት ለሰብዓዊ መብት መከበር የበኩሉን ሚና እንዲያበረከት ለማስቻል ሲሆን በተግባርም ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄዎችን በጋራ በማፈላለግ በጉዳዩ ላይ የጋራ ርብርብ ለማድረግ እንዲሁም ያሉትን መልካም ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማጋራት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

ሥልጠናው በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በሰብዓዊ መብቶች መሰረታውያን መርሆች፣ ምንጮቻቸው፣ መገለጫ ባህሪያት፤ መብቶቹን ማክበር፣ ማስከበር እና ማሟላት ሂደት የመንግሥት ግዴታ፤ በህገ-መንግስቱ እውቅና ያገኙ መብቶች፤ የሰብዓዊ መብቶች ፋይዳ ፤ በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብቶች፤ የሕግ የበላይነትና መሠረታዊ የሆኑ የፍትሕ ሂደቶችን ማጠናከር በሚሉ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነበር፡፡

ከሥልጠናው መለስ ሰልጣኖች ከምርመራ ጀምሮ እስከ ማስቀጣት እንዲሁም ከማረም እና ማነፅ ሂደት ጋር በተጨባጭ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና እየተወሰዱ ያሉ የመፍትሔ እርምጃዎች ምን እንደሚመስሉ አንስተው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡

Tagged Under: amharic Capacity Building civil liberties constitutional rights correctional services dawa denmark dire Dire Dawa Due Process fundamental rights human Human Rights investigative procedures Legal Training National Police Police Training prison prison reform reform Rights Rule of Law Suspect suspect rights Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች