በሴቶችና ሕጻናት ላይ ሚፈጸሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን ጾታን ወይም ዕድሜን መሠረት ባደረገ ተጋላጭነት በሰው ሕይወት፣ አካልና ጤንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ በሰው ነጻነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ በመልካም ጸባይ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀጽ 3፣ 4 እና 7 ላይ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲሁም ከሌሎች ወንጀል ጉዳዮች ጋር በተደራቢነት የተፈጸመ ወንጀል ሆኖ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የተፈጸመው ወንጀል ከፍተኛ ቅጣት የሚያስቀጣ ወንጀል ምርመራን የመደገፍና ጉዳዩን በዋናነት በመያዝ በፍርድ ቤት ተከራክሮ የማስወሰን እንዲሁም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚታዩ ጉዳዩችንም ክትትልና ድጋፍ ከተጣሉበት ኃላፊነቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡