የ6 ወር ህፃን ልጁን አንቆ የገደለው ግለሰብ በጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

Man Sentenced to Rigorous Imprisonment for Strangulating His 6-Month-Old Child

ዳዊት ሰለሞን ወርቁ የተባለ ተከሳሽ በ6/2/2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 5፡00 ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ማንጎ ጨፌ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር 6 ወር የሆነውን ህፃን ልጁ ሟች ፍራኦል ዳዊት አሞት እያለቀሰ ሲያስቸግረው አንገቱን አንቆ በመያዝ ሕይወቱ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ አስከሬኑን በማዳበሪያ ውስጥ በመክተት ቆሻሻ መጣያ ቦታ በመጣሉ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ 540 መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ሁለት የመከላከያ ምስክሮች በማቅረብ ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

Tagged Under: ababa • addis • addis ababa police commission • capital punishment • child • Child Abuse • child murder • commission • court • court ruling • district • federal • Federal High Court • high • Homicide • imprisonment • Infanticide • lideta • lideta district • Murder • murder conviction • nefas silk lafto sub-city • Police • rigorous • Rigorous Imprisonment • Sentencing • severe penalty • strangulation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች