ከሌላ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለሽ በሚል ምክንያት የትዳር አጋሩን የገደለው ተከሳሽ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

Defendant Who Killed His Spouse for Allegedly Having an Affair Sentenced to 21 Years of Rigorous Imprisonment

ስሜነህ ግርማ በለጠ የተባለ ተከሳሽ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 2፡20 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስኮ ሰፈረ ወርቅ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የትዳር አጋሩ የሆነችውን ሟች ማህሌት ፍቃዱን ከሌላ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለሽ በሚል ምክንያት በቢላዋ ጭቅላቷን፣ አንገቷን፣ ፊቷን፣ የግራ ክንዷንና ጣቷን፣ ደረቷንና ጀርባዋን በመውጋት ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ 539/1/ሀ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶት ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ቢፈቀድለትም ማቅረብ ባለመቻሉ እንዲሁም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት ተከሳሽ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: addis_abeba conviction federal_high_court Homicide infidelity jealousy rigorous_imprisonment
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች