በሌለበት የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶበት የነበረው ግለሰብ ከተሸሸገበት ተያዘ

Individual Sentenced in Absentia to Life Imprisonment Captured After Hiding

ጌታቸው አለምፀሀይ የተባለው ተከሳሽ የስራ ባልደረባው የነበረችውን የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ባለትዳር ነኝ በማለቷ በስራ ገበታዋ ላይ እያለች እያባረረ በቢላዋ በመውጋት ህይወቷ እንዲልፍ አድርጎ በሌለበት በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጥቷል፡፡

በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ላይ ተከሳሹ ሰውን ለመግደል አስቀድሞ በነበረው ሀሳብ ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሳባ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ የስራ ባልደረባው የነበረችውን ሟች ወ/ሮ መዓዛ ካሳን የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ባለትዳር ነኝ ስትለው የግድ አብረን እንሁን እያለ ሲያስቸግራት ቆይቶ ፈቃደኛ ባለመሆኗ በስራ ገበታዋ ላይ እያለች ጨካኝነቱን እና ነውረኝነቱን በሚያሳይ መልኩ እያባረረ በቢላዋ በመውጋት በደረሰባት ጉዳት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ የህክምና እርዳታ ሲደረግላት ቆይቶ ጉዳቷ በመባባሱ ህይወቷ ያለፈ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ አቅርቦበት ክርክር ተደርጎ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት፣ ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የተቀጣና ህዝባዊ መብቶቹ ለዘወትር እንዲሻሩ በሌለበት ተወስኖበት የነበረ መሆኑን በፌስ ቡክ ገፃችን ማጋራታችን ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቡን ሲያፈላልግ ቆይቶ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከተሸሸገበት በመያዝ በሕግ ጥላ ስር ሆኖ የእስራት ቅጣቱን እንዲፈፅም ወደ ማረሚያ ቤት እንዲላክ አድርጓል፡፡

Tagged Under: absentia absentia trial addis ababa police commission amhara region arrest arrest warrant Attempted Murder Capital capital punishment conviction criminal Criminal Justice Domestic Violence Federal High Court felony gondar Homicide imprisonment Justice lideta district court life life imprisonment manslaughter Murder murder conviction punishment sexual assault trial
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች