ከሟች መኖሪያ ቤት በመግባት አፏን በጨርቅ ጠቅጥቆ፣ አንገቷን አንቆ በመያዝ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ ጽኑ እስራት ተፈረደበት

Man Sentenced to Rigorous Imprisonment for Forcible Sexual Intercourse Resulting in the Death of a Victim After Forcibly Entering Her Home, Gagging Her, and Strangling Her

አላዩ ሞገስ ደሳለኝ የተባለ ተከሳሽ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 1፡30 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሽሮ ሜዳ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ የ14 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይ የምትኖርበት መኖሪያ ቤት በመግባት በጥፊ በመምታት፣ እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቅ እና አንገቷን በሁለት እጁ አንቆ በመያዝ በኃይል የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባትና አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቁ እና አንገቷን በማነቁ ምክንያት ትንፋሽ አጥሯት ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ/620/2/ሀ/ እና /3/ መሠረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

Tagged Under: Criminal Prosecution • Homicide • Rape • Sentencing • sexual assault • strangulation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች