በፍትሕ ሚኒስቴርና በክልል ፍትሕ ቢሮዎች መካከል ዉጤታማ የሆኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት በስራ ክፍል ኃላፊዎች ደረጃ በበይነ መረብ በመታገዝ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
ውይይቱን የመሩት በፍትሕ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን ሲሆኑ በሚኒስቴር መስርያ ቤቱና በክልል ፍትሕ ቢሮዎች መካከል የተቀናጀ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አሰራሮችን እውን በማድረግ ተቀራራቢ የሆነ የመፈጸም አቅም መፍጠር የስፈልጋል ብለዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለዉም በፍትሕ ዘርፉ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን፣ አፈጻጸሞችንና የሕግ ማዕቀፎችን በስፋት ለማስተዋወቅ ብሎም የህብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት በሚፈለገው ደረጃ ለማርካት ተቀናጅቶ መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በክልል ፍትሕ ቢሮዎች ያለው አሁናዊ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ተግባራት አፈፃፀም በስራ ኃላፊዎች በኩል የቀረበ ሲሆን እስከአሁን ያለው አተገባበር በአግባቡ ያልተቀናጀና የፍትሕ ዘርፉን ዉጤታማነት በሚፈለገው መልኩ ያላረጋገጠ በመሆኑ ቅንጅታዊ አስራሮችን በማጠናከርና ተቀራርቦ በመሥራት በዘርፉ ያለዉን አሠራር መቀየርና ዉጤት ማስመዝገብ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም በስራ ክፍል ደረጃ ሊያሰራ የሚችል የሥራ ዕቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ በሙሉ አቅም ስራዎችን አሟጦ መተግበር፣ ቅንጅታዊ አስራሮችን ማጠናከር፣ ሥራዎችን በተናበበ መልኩ መምራት፣ ከሙያተኛዉ ጋር በተያያዘ የሚታየዉን የክህሎት ክፍተቶች መሙላት እንዲሁም የስው ኃይልና የስራ ቁሳቁስ እጥረት ችግሮችን መፍታትና ዘርፉ በከፍተኛ አመራሩ ደረጃም በቂ ትኩረት አግኝቶ መደገፍ እንዳለበት ተገልጿል፡፡