የፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የስራ ጉብኝት አደረጉ

State Minister for Institutional Building and Reform Sector of the Ministry of Justice Visits Federal Police Commission Criminal Investigation Bureau

በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን የተመራ ልኡክ ቡድን በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በመገኘት በተቋሙ እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን በመጎንኘት ውይይት አድርጓል፡፡

በስራ ጉብኝቱም ወቅት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ክቡር ም/ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ የምርመራ ጠቅላይ መምሪያው ያከናወናቸውን የሪፎርም ተግባራትን በተለይም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና ሰብዓዊ መብትን በማክበር ረገድ በተቋሙ አማካኝነት የተገኙት ውጤቶች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በበኩላቸው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮው ያከናወናቸውን የሪፎርም ተግባራት አድንቀው ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚከናወኑ ተግባራትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸውን የገለፁ ሲሆን የሦስት ዓመት የፍትሕ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አካል የሆኑትን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ፣ ቅንጅትና ትብብርን ማጠናከር፣ ተደራሽነት እና ሌሎችም አምዶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት በትብብርና በቅንጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መግባባት ላይ በመድረስ የስራ ጉብኝትና ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: accessibility bureau Capacity Building civil liberties Collaboration commission criminal criminal justice reform dr. dr. ermiyas yemaneberhan ermiyas federal federal police commission fundamental rights Human Rights institutional Institutional Reform Investigation Justice Sector Transformation Legal Reform minister modern technology Police reform reform initiatives state state minister three-year plan yemaneberhan
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች