የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት ዕቅድ አፈጻጻም ግምገማ መድረክ ተካሄደ

Performance Review Meeting Held for Branch Offices' First Six-Month plan of the 2018 Budget Year

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት ዕቅድ አፈጻጻም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ በዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በዕቅድ ተይዘው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት መሰረት በሁሉም ስራዎች የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞችና የተስተዋሉ ውስንነቶች ተለይተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት ላይ በተሳታፊዎች ውይይት የተደረገ ሲሆ፤ በውይይቱ ምርመራቸው ተጠናቀው ከፖሊስ የቀረቡ ምርመራ መዛግብት ላይ ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ውሳዎችን በመስጠት የማጥራት ምጣኔው ከፍተኛ ውጤት ያለው መሆኑን፣ በክርክር ተግባራትም የተለያዩ ወንጀሎችን የፈፀሙ ወንጀለኞች ተገቢው ቅጣት እንዲወሰንባቸው መደረጉን፤ አቅም ለሌላቸው ዜጎች ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት መብታቸው እንዲከበር በማድረግ፤ በማረፊያ ቤት የሚገኙ የተጠርጣሪዎች ጉብኝት በማድረግ የታዩ ችግሮች ተለይተው መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ የተቻለ መሆኑ በመድረኩ ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በመስጠት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: appeal branch branch office Branch Offices Budget budget performance review budget year budget year performance budget year plan court Economic finance financial first first quarter performance review fiscal judiciary meeting office offices per performance Performance Review plan review six-month Tax year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች