በ2018 ዓ.ም አዲስ የተሾሙ የፌዴራል ዐቃቤያነ ሕግ የቅደመ ሥራ ስልጠና በማጠናቀቅ ቃለ-መሐላ ፈፀሙ

Newly Appointed Federal Prosecutors Took an Oath of Office Upon Completing Their Pre-Service Training

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም አዲስ የተሾሙ 80 የፌዴራል ዐቃቤያነ ሕግ ላለፉት 36 ቀናት ለ252 ሰዓታት ተግባር ተኮር የሆነ ቅድመ ሥራ ስልጠና ሲወስዱ ቆይተው ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደ መርሃ-ግብር ቃለ መሐላ በመፈፀም ከከፍተኛ አመራሩ የሥራ መመሪያ ተቀብለዋል፡፡

የቅድመ ሥራ ስልጠናው በዋናነት ትኩረት ካደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ተቋሙን ማስተዋወቅ፣የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የዜጎች ቻርተር፣ KPI፣ የደንበኞች አገልግሎት፣ ተግባራዊ ምልከታ፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር የወንጀል ምርመራ እና ክስ አሰራር እንዲሁም በልዩ ልዩ አዋጆች የተካተቱ ወንጀሎች (ሽብር፣ ኮፒውተር ወንጀሎች፣ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ማሰረጨት፣ በሰዎች መነገድና ሰዎችን በሕገወጥ መንግድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች፣ ሙስና፣ ታክስ፣ ጉምሩክ፣ ሀብት ማስመለስ፣ የወንጀል ሕግ መሰረታዊ ነጠሮች፣ ፣ የዐቃቤያነ ህግ ማኑዋል) ፣ የሥነ-ሥርዓት /የቀድሞ እና አዲሱ ስነ-ስርዓት ሕግ እንዲሁም የፍትሐብሔር ሥ/ሥ/ሕግ) እና የማስረጃ ህጎች፣ የወንጀል መርመራ፣ ማስረጃ ምዘና፣ ክስ ዝግጅት እና የክርክር ክህሎት፣ ይግባኝ እና ሰበር ድረስ እና የሲስተም ትውውቅ የሚገኙበት ሲሆን፣የተግባር ልምምዶች እንዲሁ መደረጋቸው ተገልፆል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን ተግባራዊ ማድረግ በጀመረበት እና አዳዲስ አደረጃጀቶችን ዘርግቶ ወደ ሥራ በገባበት እንዲሁም ባለፉት ዓመታት ሲጠበቅ የነበረው የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ በፀደቀበት በዚህ ወቅት ወደ ሥራ መሰማራታቸው የዐቃብያነ ሕጉን ሹመት ከዚህ ቀደም ከነበረው ልዩና ታሪካዊ እንደሚያደርገው የተገለፀ ሲሆን፣ እጩ ዓቃቢያነ ሕጉም ቅንነትን በመላበስ የሕግ የበላይነትንና ሰብዓዊ ክብርን መሠረት ያደረገ ተዓማኒ፣አካታች የፍትሕ ስርዓት በመገንባት ሒደት ውስጥ የፍትሕ አርበኛ በመሆን የራሳቸውን አሻራ ሊጥሉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

እጩ ዐቃብያነ ሕጎቹም በበኩላቸው የወሰዱት የቅድመ ሥራ ስልጠና ያላቸውን እውቀት ያዳበሩበትና በተለይም ተግባር ተኮር ስልጠናው ለሚቀበሉት አገራዊ ሐላፊነትና ለቀጣይ ሥራቸው ስንቅ የሚሆናቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

በመጨረሻም የተቋሙ የበላይ አመራር ባስተላለፉት መልዕክትና የሥራ መመሪያ ወቅት እንደተገለፀው፣ እጩ ዓቃቢያነ ሕጉ የሕግ የበላይነትን በፀና መሠረት ላይ ለማስቀመጥ የተቋሙን ዕሴቶች የተላበሱ ባለሙያዎች መሆን እንደሚገባቸው የተገለፀ ሲሆን፣ በፍፁም አገልጋይነት መንፈስ ሰው ተኮር የሆነ ስራን በመስራት ፣በቅንነት፣ ለለውጥ በመትጋት፣ለልሕቀት በመበርታትና በሕብረት በመፍጠን በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና በስራ ሂደት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በማለፍ ለላቀ ለውጥ እንዲተጉ በታላቅ አደራ አሳስበዋል።

Tagged Under: academic african charter on the rights and welfare of the child attorney Capacity Building constitution of the federal democratic republic of ethiopia Convention on the Rights of the Child e-service ecu Education federal lawyer learning legal counsel new oath oath of office office office of the federal auditor general point pre-service pre-service training pro Prosecutor Prosecutors school Service Training vice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች