የፍትህ ሚኒስቴር ከUNODC ጋር በመተባበር በተቋሙ አዲስ ለተቀጠሩ ዐቃቢያነ ህግ በሰዎች መነገድና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን አስመልክቶ ተግባር ተኮር ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል

Ministry of Justice, in Collaboration with UNODC, Provides Practical Training to Newly Recruited Prosecutors on Human Trafficking and Smuggling of Migrants

ሰኔ 12/2016 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር አዲስ ለተቀጠሩ ዐቃቢያነ ሕግ በሰዎች መነገድና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን አስመልክቶ ተግባር ተኮር ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ፣ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ በሥልጠና መድረኩ ተገኝተው በሰዎች መነገድና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ዓለም ዓቀፍ ትስስር ያለው ፣ከፍተኛ በሚባሉ ሰዎች የሚዘወር ፣በወንጀል ገቢ ሁኔታ ሁለተኛ ደረጃን የሚይዝና በሚያመነጨው ኢኪኖሚያዊ አቅም መንግስታትን የሚገዳደር መሆኑን አውስተዋል፡፡

ወንጀሉን ለመከላከል አገራችን የተቀበለቻቸውን ዓለም ዓቀፍ ህጎችን ተግባራዊ በማድረግ ፣ የተለያዩ አገር አቀፍ ህጎችን በማውጣት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ቢሰጥም ወንጀሉ ከመቀነስ ይልቅ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለው እንዳሉት ወንጀሉ ከመፈፀሙ በፊት መከላከል ፤ወንጀሉ ተፈፅሞ ሲገኝ ግን የወንጀሉን ባህሪና አስከፊነት ተረድተን በወንጀል ተሳትፈው የተገኙ ወንጀለኞችን በወንጀላቸው ልክ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ይጠበቅብናል ያሉት ሲሆን ሥልጠናው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሰዎች መነገድና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን አስመልክቶ የታዩና ውሳኔ ያገኙ መዝገቦች እንዲሁም ተግባር ተኮር ሥልጠና ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሥልጠናው ለሶስት ቀን የሚሠጥ ሲሆን ሥልጠናውን የሚሰጡት በዳኝነት ዓለም ዓቀፍ ልምድ ያላቸውና አሁንም የዳኝነት ስራቸውን እየሰሩ ያሉና በተጨማሪ UNODCን በአማካሪነት እያገለገሉ ያሉት ሚስተር ኤርዋን ቶር ይሆናሉ፡፡

Tagged Under: anti-trafficking • border • border crossing • Capacity Building • case studies • Crime Prevention • criminal • Criminal Justice • crossing • Education • human • Human Trafficking • international • International law • Justice • learning • legal • Legal Training • migrant • Migrant Smuggling • practical training • Prosecutors • skill development • Smuggling • trafficking • Training • Transnational crime • UNODC
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች