የውጭ አገር ዜጎች የቤት ባለቤትነትን ለመደንገግ በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

Discussion Held with House of Peoples' Representatives Standing Committee Members on the Draft Proclamation to Regulate Home Ownership for Foreign Nationals

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ እና የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተሳተፉበትና ትኩረቱን የውጭ ሀገር ዜጎች የቤት ባለቤትነትን ለመደንገግ በወጣው ረቂቅ አዋጅ ያደረገ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ክርብት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ ተገኝተው በረቂቅ አዋጁ ላይ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል። በውይይቱ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ክርብት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት እንደ መንግሥት ለራሳችን ዜጎች የምንሰራቸው የተለያዩ ልማቶች እንዳሉ ሆነው፣ በሌላ በኩል ከተቀረው አለም ጋር ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችሉንን የሕግ ማእቀፎችን ማዘጋጀት እና አሰራሮችን መዘርጋት ስለሚያስፈልግ አዋጁ መዘጋጀቱን እና ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ሰፋ ያሉ የውይይት መድረኮችን በማካሄድ የጋራ የሆነ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ ባቀረቡት የመድረክ የመወያያ ሰነድ ላይ ረቂቅ አዋጁ ለኢኮኖሚው ዘርፍ ያለውን አዎንታው አንደምታ፣ ጠቅለል ያለ ይዘቱን እንዲሁም ቀደም ሲል ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና ከሕዝብ ተወካዮች እንዲሻሻሉ በአስተያየት የተነሱ ነጠቦችን አካተው ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በዚህም ወቅት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በርካታ ጥብቅ የሚባል ሕግ የነበራቸው ሀገራት ሕጋቸውን በማሻሻል ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር እራሳቸውን አስተካክለው ተጠቃሚ መሆናቸውን ክብርት ሚኒስትሯ ጠቁመው፤ ከዚህ አንፃር አዋጁ ከመዘጋጀቱ ቀደም ብሎ ግብፅ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ቬትናም፣ ቻይና ያላቸውን ተሞክሮ ለማየት ጥረት መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

አክለውም በአጠቃላይ የውጭ ሀገር ዜጎች የቤት ባለቤትነትን ለመደንገግ የሚያስችለውን አዋጅ ማውጣት ካስፈለገበት አበይት ምክንያቶች መካከል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ተሳታፊና ተወዳዳሪ ሆኖ መቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ፣ የሀገርን የውጭ ምንዛሪ አቅምን ማሳደግ ስለሚያስችል፣ ይህ አዋጅ ፀድቆ በስራ ላይ ከዋለ ወደ ሀገር ቤት የሚጣውን የካፒታል ፍሰት የሚያበረታታ፣ የሪል ስቴት ዘርፉን የሚያነቃቃ እንዲሁም እንደ ሀገር አዎንታዊ የኢንቨስትመንት ምልከታ እንዲኖር ስለሚያደርግ አዋጁን እጅግ አስፈላጊ እንደሚያደርገው አስገንዝበዋል፡፡

የዛሬውን ጨምሮ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከሕዝብ ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በተከታታይ በነበሩ የውይይት መድረኮች ላይ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶች እንዲሁም ጥያቄዎች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጁ ይዘት ላይ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር በመቻሉ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: amharic capital inflow China committee draft Draft proclamation Economic development egypt foreign foreign direct investment home house house of peoples’ representatives international best practices kenya legal framework legislative process ministry of urban development and construction National nigeria ownership peoples' proclamation real estate investment Representatives Stakeholder Consultation standing standing committee
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች