ወንጀልን በመከላከል ረገድ የማህበረሰቡን ሚና በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የንቃተ ህግ ግንዛቤ በመሰጠት ላይ ይገኛል

Legal Awareness on the Role of the Community in Crime Prevention Being Provided to Residents of Addis Ababa City

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀና ወንጀልን ለመከላከል የማህበረሰቡ ሚና በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ለከተማው ነዋሪዎች መሰጠት ተጀምሯል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል መከላከልን እና የህብረተሰቡን የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ለመፍጠር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረትም ከህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚሰጠው የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ከቂርቆስ እና ከልደታ ክፍለ ከተሞች የተወከሉ ነዋሪዎች በተገኙበት በከተማ አቀፍ የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ፈጠራ ሲጀመር መድረኩ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ መድረኩን በመክፈት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ሥልጠና ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዳልካቸው ወርቁ ወንጀልን መከላከል ያለ ማህበረሰቡ ተሳትፎ የማይሳካ መሆኑን ጠቅሰው ሥልጠናው በዋነኝነት ወንጀል ጠል የሆነ ማኅበረሰብ እንዲፈጠር የማድረግ እንዲሁም የንቃተ-ሕግ ደረጃውን ከፍ ያለ ማኅበረሰብ የመፍጠር ዓላማ ያለው ሥልጠና መሆኑን አስታውሰው፤ መንግሥት እየወሰደ የሚገኘውን ሕግ የማስከበር ተግባር እንዲሁም ወንጀልን የመከላከል ስራ ውጤታማ ማድረግ የሚቻለው ህዝቡ ተሳታፎ ማድረግ ሲችል ብቻ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የንቃተ ሕግ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኩ ላይ ተገኝተው በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ፋሲካ ፈንታ በበኩላቸው ወንጀልን በመከላከል ረገድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እያደረጉ ለሚገኙት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን ገልፀው፤ ህብረተሰብን የማያሳትፍ የወንጀል መከላከል ስራ ውጤታማ ስለማይሆን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተመሳሳይ የሥልጠና መድረኮች ተዘጋጅተው ማህበረሰቡ ያለውን ወንጀልን የመከላከል ሚና የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ መምጣታቸውን የተናገሩት የሥልጠና ተሳታፊ አቶ ሀብቴ ተክለ ማሪያም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መካሄዱ በመኖሪያ አካባቢያችን ሄደን ያገኘነውን ግንዛቤ ለሌሎች ለማካፈል እንዲሁም በሥልጠናው ላይ ባገኘነው ግንዛቤ መሠረት ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸሙ በመምከር እና በመገሰጽ ሌሎችን ወንጀል እንዳይፈፅሙ በማድረግ የራሳችንን አስተዋፅኦ እንድናበረክት የሚያግዝ ሥልጠና አግኝተናል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከልደታ ክፍለ ከተማ የመጡት አስመራወርቅ ዘሪሁን የተባሉ ተሳታፊ በበኩላቸው ሥልጠናው ውጤታማ እንደነበር ገልፀው፤ ሥልጠና እየተዘጋጀ ለህብረተሰቡ በዚህ መልክ መስጠት ቢቻል በየአካባቢው ላይ ወንጀል ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡

የንቃተ-ሕግ ግንዛቤ ፈጠራ ምድረኮቹ እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማዎች ቀጥለው የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

Tagged Under: ababa addis addis ababa addis ababa police commission Awareness citizen commission community Community Engagement Community Policing Crime Crime Prevention Criminal Justice democratic FDRE federal federal democratic republic of ethiopia (fdre) kirkos sub-city legal Legal Awareness Legal Education lideta sub-city Police policing prevention public awareness campaign republic training programs workshops
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች