በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት በተቋሙ ለሚገኙ መካከለኛ አመራሮች የስራ አመራር ክህሎት ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት በተቋሙ የሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች እውቀት እና ክህሎት ለማሳደግ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሥልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ በማስታወስ አመራሮች በስራ አመራር ላይ ያላቸውን ክህሎት በማዳበርና ስራን በተገቢው ሁኔታ በመምራት የህብረተሰቡን የፍትሕ ጥያቄ መመለስ ይቻል ዘንድ ይህ ሥልጠና እንደተዘጋጀ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ አያሌው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በስራ ትጋታቸው እና አፈፃፀማቸው ወደ መካከለኛ አመራርነት ለመጡት አመራሮች ሥልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ነባር አመራሮች ደግሞ ልምዶቻቸውን የሚያጋሩበት እና አቅምና ችሎታቸውን የሚያድሱበት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ሥልጠናው ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በውሳኔ አሰጣጥ እና ችግር አፈታት፣ በተግባቦት እና በዕቅድ አወጣጥ እና ስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡