በዓለምዓቀፍ የውል ዝግጅት እና ድርድር ዙሪያ ለተከታታይ 5 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ

Five Day Training on International Treaty Drafting and Negotiation Concludes


የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ /TDB Group/ ጋር በመተባበር በዓለምዓቀፍ ውል ዝግጅትና ድርድር ሂደቶች ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ሥልጠና መጠናቀቁ ተመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግን ጨምሮ ከ21 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉበትና ከሐምሌ 21 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የነበረው በዓለምዓቀፍ የውል ዝግጅትና ድርድር ዙሪያ ያተኮረው ሥልጠና ተጠናቋል፡፡

በሥልጠናው ድንበር ተሻጋር ውሎችን ከመደራደር አንጻር የሚታዩ ክፍተቶችና ተቋማት ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የድርድር ስልቶች፣ የተለያዩ የግንኙነት ዘዴዎች(communication methods)፣ የባህል ልዩነት በውል ድርድሮች ላይ ያለው ተፅዕኖ፣ በውሎች የሚካተቱ ድንጋጌዎች የሕግ ማውጣት ነጻነትን ከማስጠበቅ አንጻር (stabilization Clauses) ሊወሰዱ ስለሚገቡ አማራጮች፣ ከውል ጋር የተያያዙ ስጋቶችን ከመቅረፍና ስለማስተካከል(allocation of risk)፣ ከመንግሥትና የግል አጋርነትን ጨምሮ የሚገቡ ስምምነቶች መደረግ የሚገባቸው ዝግጅቶች እንዲሁም ኢንቨስትመንቶችን ተከትሎ የሚመጡ የውል ድርድር አመራርና አገራዊ ሕጎች ይዘት እንዲሁም የፕሮጀክት ውሎች ድርድር አመራር ዙሪያ በተግባር የተደረፈ ልምምድ ተደርጓል፡፡

በሥልጠናው መዝግያ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርሚያስ የማነብርሐን{ዶ/ር} ባስተላለፉት መልዕክት በሥልጠናው ሂደት የተገኘው እውቀት በቀጣይነት የሚኖሩ ሥራዎችን ለመጀመር የሚያስችል መነሻ ክህሎት የተገኘበት በመሆኑ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በያሉበት ዘርፍ ላይ ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው በቀጣይነት በተሻለ ደረጃ የአገርን ጥቅም የሚያስጠብቁ ሥራዎችን መሥራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ይሕ ልዩ የሆነ ሥልጠና በተገቢው መንገድ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ያደረጉ አካላትን ማለትም Trade and development bank group(TDB Group)፣ African Legal Support Facility (ALSF), New Perimeter፣ DLA PIPER እና ሌሎች ተባባሪ አካላትን አመስግነዋል፡፡

በመጨረሻም በሥልጠናው ላይ በመገኘት በዓለምዓቀፍ የቢዝነስ ውል ዝግጅትና ድርድር ዙሪያ ለአምስት ቀናት የተሰጠውን ሥልጠና ለተከታተሉ የሕግ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶ ዝግጅቱ ተጠናቋል።

Tagged Under: Africa african allocation ban bank communication day development draft drafting facility group ica international International Treaty legal Legal Support meter National negotiation new per port rea risk stabilization support Trade Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች