የፍትሐ ብሔር ፍትሕ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጀነራል

የፍትሐ ብሔር ፍትሕ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጀነራል በመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን የፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤትን በመወከል የፍትሐ ብሔር ክስ በመመስረት፣ ክርክር በማድረግ እና አቅጣጫ በመስጠት፣ በግዙፍ የመንግሥት ፕሮጀክቶች የውል ዝግጅት እና ድርድር በመሳተፍ፣ የኢፌዲሪ መንግሥትንና ተቋማቱን በዓለምአቀፍ የዳኝነትና ከፊል ዳኝነት አካላት በሚከሱበት ወይም በሚከሰሱበት ጉዳይ መንግሥትን በመወከል ክርክር እና ድርድር በማድረግ እንዲሁም በፍትሐ ብሔራዊ ጉዳዮች መንግሥትንና የመንግሥት ተቋማትን በማማከር የሕዝብና የመንግሥትን ፍትሐ ብሔራዊ ጥቅም ያስጠብቃል፡፡ በተጨማሪም የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው በአዋጅ ቁጥር 1263/14 አንቀጽ 40 (2) (ሀ) መሠረት የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸው ባልተግባቡበት የፍትሐ ብሔር ጉዳይ ላይ ውሳኔ ይሰጣል እንዲሁም የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያንንና የወንጀል ተጎጂዎችን ወክሎ መከራከር ከተጣሉበት ኃላፊነቶቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ሔኖክ ተስፋዬ ተፈራ

ዳይሬክተር ጄነራል

News From Civil Justice Administration Directorate General