በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ውስጥ በስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ተግባራት አፈፃፀም በሚመለከት በተደረገ ምልከታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

Discussion Held on Observation Findings Regarding the Performance of Ethics and Anti-Corruption Activities within the FDRE Ministry of Justice and its Subsidiary Institutions

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና በስሩ በሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ላይ በ2017 በጀት ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት በስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ተግባራት ዙሪያ የነበረውን አፈፃፀም አስመልክቶ በምልከታ በተገኙ ውጤቶች እንዲሁም በቀጣይነት በሚጠበቁ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዚህ የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው በተቋማቱ ውስጥ በስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ረገድ በተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ዙሪያ የተገኙትን የምልከታ ውጤቶች ሪፖርት ያቀረቡት የምልከታ ቡድኑ አሰተባባሪ አቶ ሰጠኝ አዲሱ ሲሆኑ፤ በዚህም አጠቃላይ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ተግባራት የሚገኙበትን ደረጃ ለመገምገም የሁሉም ተቋማት ተወካዮች ተካተው እንዲቋቋም በሚደረግ ስራ አማካኝነት በዓመት 4 ጊዜ ምልከታ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የምልከታው ዋና ዓላማ በተቋማቱ ውስጥ በተከናወኑ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ተግባራት የተገኙ የተሻሉ አፈፃፀሞችን አጠናክሮና አስፋፍቶ ማስቀጠል የሚቻልበትን አቅጣጫ ለማመላከት እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ደግሞ በቀጧይነት የተሻለ ስራ ማከናወን የሚቻልበትን መንገድ በመጠቆም እገዛ ማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለውይይቱ መነሻ የሆነው በ2017 በጀት ዓመት በ4ኛ ሩብ ዓመት ውስጥ በስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ረገድ በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች እንዲሁም በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ውስጥ በተደረገው ምልከታ ወቅት የተገኙ ውጤቶችን ቀርበዋል፡፡ በዚህም መሠረት ተቋማቱ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ክፍሎችን ማደራጀታቸው፣ የበላይ አመራሩ በስራው ላይ ድጋፍ በማድረግ የሚሳተፍ መሆኑ እንዲሁም የአመራሩንና የሰራተኞችን የሀብት ምዝገባ በማድረግ መረጃ መያዝ መቻላቸው በጥንካሬ ከተገለፁት አፈፃፀሞች መካከል የጠቀሱ ሲሆን፤ በሌላም በኩል ተቋማቱ የተሟላና አመቺ የሆነ የስራ ቦታ የሌላቸው መሆኑ፣ የባለሙያ እጥረት ፣ ውሳኔ ለሚፈልጉ ስራዎች በወቅቱ ፈጣን ምላሽ አለመስጠት እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በክፍተትነት የተለዩ መሆናቸውን በማካተት የምልከታ ሪፖርቱን በዝርዝር ቀርቡዋል፡፡

የምልከታ ሪፖርት ተከትሎ በተቋማቱ ተወካዮች በኩል ምላሽና አስተያየቶች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም ወቅት በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መዝሙር ያሬድ የፌደራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም ምልከታ በማድረግ እንዲሁም የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት በዘርፉ ላይ ለሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር እንዲሁም በተጠሪ ተቋማት ላይ በተደረገው ምልከታ መሠረት መልካም አፈፃፀሞችን በማጠናከር እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን ትኩረት ሰጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲስተካከሉ በማድረግ በቀጣይነት የተሻለ ስራን ለማከናወን የሚመለከታቸው አካላት ጥረት ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: Anti-Corruption • Capacity Building • certification • compliance • correctional • corruption prevention • democratic • Documents • Ethical conduct • ethics • FDRE • federal • federal democratic republic of ethiopia (fdre) • Good Governance • institutions • monitoring • observation • performance • performance gaps • performance monitoring • professional development • reform • registration • report • republic • stakeholder meeting • training programs
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች