ለመካከለኛ አመራሩና ዐቃቢያነ ሕግ በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ

Capacity Building Training Provided for Mid-Level Leaders and Legal Managers in Project Management

ከፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የማስፈጸም አቅም ለመገንባት በተቋም ደረጃ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ተግባራት መካከል የአመራሩንና የዐቃቢያነ ሕግን የመፈጸም አቅም መገንባታ አንዱ ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትኩረቱን በፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮጀክት አሰተዳደር ላይ ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በተቋሙ ለሚገኙ መካከለኛ አመራሮችና ዐቃቢያነ ሕግ ተሰጥቷል፡፡

ሥልጠናው ከየካቲት 08 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ የተሰጠ ሲሆን የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኖህ ታከለ በመክፈቻ ንግግራቸው “መካከለኛ አመራሩና ዐቃቢያነ ሕግ ከፕሮጀክት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ያሉ መሠረታዊ ነጥቦች ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ እንዲጎለበትና በፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ሥራዉ ከዕቅድ ማቀድ ጀምሮ የሚፈለገዉን ዉጤት እስከ ማስመዝገብ ድረስ ያለዉን ሂደት በተለይ ከፕሮጀክት አስተዳደር መርህ አንጻር መቃኘት እንዲቻል ሥልጠናው ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል” ብለዋል፡፡

ሥልጠናው በተለይም ከፍትሕ ሥርዓቱ ጋር ተያይዞ ችግር ፈቺ ዕቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ ዉጤት ተኮር የሆነ ክትትልና የውጤት ግምገማ እስከ ማድረግ እንዲሁም በሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ዙሪያ ዓለም ዓቀፍ የሆኑ መስፈርቶችን መቃኘት በሚያስችል ደረጃ ተዘጋጅቶ የተሰጠ ሲሆን የሥልጠናው ተሳታፊዎችም ሥልጠናዉን በማግኘታቸው የተሻለ የሥራ አቅምና ተነሳሽነትን የፈጠረላቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

በሥልጠናው መዝጊያ ንግግር ያደረጉት የፍትሕ ሚኒስተሩ ከፍተኛ አማካሪና የጥቆማ እና ቅሬታ ማስተናገጃ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ምስክር ታሪኩ በበኩላቸው ሥልጠናው ተቋሙ እየተገበረ ባለው የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ በተለይም የአመራሩንና ዐቃቢያነ ሕግ የመፈጸም አቅም ለማሳድግ ታስቦ የተሰጠ መሆኑን ግልጸው ሰልጣኞች ከሥልጠናው ባገኙት ዕውቀት ተጠቅመው ዉጤታማ አፈጻጸም እንደሚያስመዘግቡ ያላቸውን እምነት የገለጹ ሲሆን መሰል የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችም በየደረጃዉ እንደሚሰጡ በመጠቆም ሥልጠናዉን በማዘጋጀት ረገድ ትብብር ያደረገዉን Feteh (Justice) Activity IN ETHIOPIAን አመስግነዋል፡፡

Tagged Under: Capacity Building
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች