የቅሬታ ማስተናገጃ ጽ/ቤት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሥር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን በዘርፉ ሥር ባሉ የሥራ ክፍሎች በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ በመመርመር ውሳኔዎች በሕግ እና በማስረጃ መሠረት መወሰናቸውን በማረጋገጥ ተገቢው ውሳኔ እንዲሰጥባቸው የውሳኔ ሃሳብ ለዘርፉ ሚኒስትር ዲኤታ በማቅረብ የዜጎችን መብት ማስከበር ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
