ምስክር ታሪኩ በፍትሕ ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ከየካቲት 2014 ዓ.ም ጀምሮ በማገልገል ላይ ይገኛል። በዚህ ኃላፊነት ማገልገል ከመጀመሩ አስቀድሞ የሚኒስትሩ የቅሬታ እና አቤቱታ መስተንግዶ ጽ/ቤት፣ ኃላፊ፣ የሕግ ማስፈጸም ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የፍትሐብሔር ፍትሕ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና ምክትል ኃላፊ እንዲሁም ጀማሪ ዐቃቤ ሕግ በመሆን ከሕዳር 2002 ዓ.ም ጀምሮ በፍትሕ ሚኒስቴር አገልግለዋል። ከ15 ዓመት በላይ ባካበቱት ልምድ በኢትዮጵያ የሕግ የበላነት እንዲረጋገጥ እና ፍትሕ እንዲሰፍን በቁርጠኝነት ለማገልገል ዝግጁ ናቸው።