በፍትሃብሔር ሥራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ተሰጠ

A training focused on civil works was given

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ድሬዳዋን ጨምሮ ከሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የተዉጣጡ የፍትሃብሔር ተጠሪ ዓቃቢያነ ሕግ የተሳተፉበትና ትኩረቱን በፍትሃብሔር ሥራዎች ላይ ያደረገ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናዉ ዋና ዓላማም በፍትሃብሔር ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ዓቃቢያነ ሕግ በዘርፉ ያላቸዉን ዓቅም መገንባት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በሥልጠናዉ በዋናነት የፍትሃብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጉ ላይ እና በተቋሙ የሚሰሩ ሌሎች የፍትሃብሔር ሥራዎች ማለትም የሕግ ምክር፣ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት፣ ክስ ዝግጅት እና ችሎት ክርክር ብሎም ሌሎች የመንግሥት ተቋማትን በመወከል በሚሰሩ ፍትሃብሔራዊ ስራዎች ላይ ያሉ የአሠራር ስርዓቶች ተዳሰዉበታል፡፡

ስልጠናዉ በፍትሕ ሚኒስቴር የሚሰሩ ዐቃቢያነ ሕግን ዓቅም ለማጎልበት ታስቦ በክረምት ልዩ የስልጠና መርሐ ግብሮች ከተያዙ ስምንት ስልጠናዎች ዉስጥ ሰባተኛዉ ሲሆን በቀጣይም በልዩ ስልጠናዉ በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት የመጨረሻ የሆነዉ ስልጠና እንደሚሰጥ ተጠቋሟል፡:

Tagged Under: academic • administrative training • agency for civil society organizations • agricultural training • amharic civil procedure code • anti-corruption training • arbitration training • awareness training • Capacity Building • capacity building training • charity work • civil • civil and political rights • civil appeals • civil asset forfeiture • civil aviation • civil aviation authority • civil aviation proclamation • civil cases • Civil Code • Civil Code amendment • civil contempt • Education • learning • school • Training • Use • used • work • works
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች