መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከሀገር ሲወጡ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ የሚያስችል የቅብብሎሽ መግባቢያ ሰነድ የፊርማ ስነ ስርዓት ተካሄደ

A memorandum of understanding facilitating the repatriation of citizens who have left the country through irregular means has been signed.

በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት፣ ከዓለም የፍልሰት ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር በተዘጋጀ ብሔራዊ የፍልሰት ምክር ቤት ዓመታዊ መድረክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የፍልሰት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባሉበት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከአገር ሲወጡ የሚያዙ ዜጎችን ተጋላጭነት በመቀነስ ሰብዓዊ ክብራቸውን ጠብቆ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው እንዲመለሱና ለዘለቄታው እንዲቋቋሙ ለማድረግ የሚያስችል የቅብብሎሽ መግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡

ጉዳዩ የሚመለከታቸው 6 የፌዴራል ተቋማት፣ 12 ክልሎችና 2 የከተማ መስተዳድሮችን ወክለው በተገኙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አማካኝነት የተፈረመውን የቅብብሎሽ የስምምነት ሰነድ ይዘቶችን በማስመልከት አስተያየት የሰጡት የትብብር ጥምረት ሴክሬታሪያት ኃላፊ የሆኑት አቶ አብረሀም አያሌው በርካታ ፍልሰተኞች በየአመቱ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ድንበር አቋርጠው ሲወጡ በፌዴራልና በክልል የፀጥታና የሕግ አካላት ለሚያዙ ዜጎች ከምግብና ከጊዜያዊ ማቆያ ጀምሮ አስቸኳይ የሆነ የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ ፈታኝ መሆኑን ተናግረዋል፤ አክለውም ለዚህ ጉዳይ ተብሎ በፀጥታና የሕግ ተቋማቱ የሚያዝ በጀት ባለመኖሩ ትራንስፖርት ለማቅረብ አለመቻል፤ በፌዴራል ተቋማት እንዲሁም በመተላለፊያ፣ በመውጫና በመድረሻ ክልሎች መካከል ቅንጅትና ትብብር አለመኖር ሂደቱን አስቸጋሪ አድርጎት መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም ችግሩ ከሕግ አስከባሪ አካላት አቅም በላይ እየሆነ በመሄዱ ተጎጂዎች ለዳግም ፍልሰት ብሎም ለሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች የሚጋለጡበት ሁኔታ እየተከሰተ በመሆኑ በመላው የአገሪቱ አቅጣጫዎች በቅንጅት መሥራት የሚያስችል ስምምነት ማድረግ ማስፈለጉን አስረድተዋል፡፡

የጋራ ቅንጅትን የሚፈልገውን የፍልሰት ጉዳይ ለማሻሻል እንዲያግዝ ታሳቢ ተደርጎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የፍትሕ ሚንስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሀና አርዓያስላሴ እንዲሁም የፌዴራል፣ የከተማ መስተዳድሮችና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቀርበው ፍልሰተኞችን ሰብዓዊ ክብራቸውን ጠብቆና መሠረታዊ አገልግሎቾችን አሟልቶ ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ በሚያስችለው የቅብብሎች መግባባቢያ ሰነድ የስምምነት ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

በመጨረሻም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የፍልሰት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሰነዱን አተገባበር አስመልክቶ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ሁሉም አካላት በትኩረት መፈጸም እንደሚገባቸው የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Tagged Under: adama science and technology university Addis Ababa Science and Technology University addis ababa water and sewerage authority african charter on human and peoples’ rights african charter on the rights and welfare of the child african commission on human and peoples' rights and cultural rights and healthcare administration and healthcare administration and control authority and medium enterprises (msmes) citizen citizens Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) country iom irregular medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 memorandum Memorandum of Understanding memorandum of understanding (mou) repatriation standing standing committee on law and justice technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet) un un convention on the rights of the child understanding
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች