የተደራጁ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ስር የሚገኝ የስራ ክፍል ሲሆን የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንጀሎችን፣ ሕገመንግሥት እና ሕገመንግስታዊ ስርዓት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀል ጉዳዮችን፣ ዓለምአቀፍ ሕጎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀል ጉዳዮችን፣ የሽብር እና የኮምፒዩተር ወንጀሎችን ምርመራ የመምራት፣ መንግሥትን ወክሎ ክስ አቅርቦ የመከራከር እና ዉሳኔ የማስፈፀም ኃላፊነት የተሰጠዉ ስራ ክፍል ነዉ፡፡
