ለሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 236 ሚሊዮን 400 ሺ ኤስ.ዲ.አር /ሁለት
መቶ ሰላሣ ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር/ መደበኛ ብድር እና ከስኬል-አፕ ፋሲሊቲ ክሬዲት 125 ሚሊዮን አሜሪካን ዶላር /አንድ መቶ ሃያ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር/ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለምዐቀፍ የልማት ማህበር መካከል መጋቢት 29 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 15 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፤-
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•