ለሁለተኛው አገር አቀፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ሃይጂን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 243 ሚሊዮን 750 ሺህ (ሁለት መቶ አርባ ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) የሳዑዲ ሪያል የሚያስገኘው የብድርስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በሳዑዲ የልማት ፈንድ መካከል ታህሳስ 9 ቀን 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡