በአገልግሎት ላይ

ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ አርባ አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር (41 ሚሊዮን 300 ሺህ) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት አና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል እ.ኤ.አ አፕሪል 3 ቀን 2020 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1190/2012
ቀን: ሚያዚያ 14፥ 2012 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች