በአገልግሎት ላይ

ለሰው ሀብት ልማት ኦፕሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውል ብድር ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

ለሰው ሀብት ልማት ኦፕሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውል 37 ሚሊዮን 200 ሺህ ኤስ.ዲ.አር. (ሠላሳ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር) ብድር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በአካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1301/2016
ቀን: ታህሳስ 10፥ 2016 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

ደንብ ቁጥር 537/2015

ነሐሴ 22፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1182/2012

መጋቢት 4፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ