ለከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ 96 ሚሊዮን 900 ሺ ኤስ.ዲ.አር. (ዘጠና ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር.) ብድር የሚያስገኘው የፋይናንስ ስምምነት ማሻሻያና ክለሳ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል እ.አ.አ ጁን 12 ቀን 2012 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 4 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•