ሕዝቦች በሰላም፣ በነጻነትና በተረጋጋ ሁኔታ ለመኖር ያላቸው መብት ከሽብርተኝነት አደጋ ሁል ጊዜ መጠበቅ ያለበት በመሆኑ፤
ሽብርተኝነት ለሀገራችን ሰላም፣ ደኅንነትና ዕድገት ፀር እንደሆነ፣ ለአካባቢያችንና ለዓለም ሰላም እና ደህንነትም ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ ግንዛቤ የተወሰደ በመሆኑ፤ በስራ ላይ ያሉት የሀገሪቱ ሕጎች በበቂ ሁኔታ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ባለመሆናቸው ጠንካራ የሕግ አቅም መፍጠር በማስፈለጉ፤ ሽብርተኝነትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ለማምከን በቂ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጠናቀር፣ በሽብርተኝነት የተጠረጠሩ ሰዎችን ወይም ድርጅቶችን ለሕግ ለማቅረብ የሚያስችሉ የተጠናከሩ የምርመራና ክስ የማቅረብ አዳዲስ ስልቶችንና ስርዓቶችን በሕግ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤
ሽብርተኝነትን በሚገባ ለመዋጋት የፀረ-ሽብርተኝነት ዓላማ ካላቸው የአካባቢያችን፣ የአሕጉራችንና የሌላው የዓለም ክፍሎች መንግስታትና ሕዝቦች ጋር መተባበር እና በተለይ ከተባበሩት መንግስታትና ከአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ጋር የተደረጉትን ስምምነቶች ስራ ላይ ማዋል አስፈላጊነቱ የታመነበት በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•