የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ 86 (5) ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ጋር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚያዊ ኅብረትና የሕዝቦች ወንድማማችነትን ማጎልበት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት መርህ እንደሆነ በመደንገጉ፤
አገራችን ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን አጋርነት ለማሳደግ፣ ለፓን-አፍሪካኒዝምና ለአፍሪካ የውህደት አጀንዳ ተግባራዊነት ያላትን ቁርጠኝነት ለማስቀጠል እንዲሁም የሕብረቱ ኮሚሽን አስተናጋጅ አገርነት ሚናዋን ለመወጣት ከምታከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማን ማውለብለብ፣ የአፍሪካ ሕብረት መዝሙርን ማዘመር እና የአፍሪካ ቀን ታስቦ እንዲውል ማድረጉ አገራችን ለሕብረቱ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ በመሆኑ፤
በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሕብረቱ ሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር በአባል አገራት እንዲውለበለብ እና እንዲዘመር እንዲሁም የአፍሪካ ቀን እንዲከበር ያስተላለፈውን ውሳኔ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ፤
ይህንኑ ስምምነተ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•