የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ26ኛው የመሪዎች ጉባዔ እኤአ ጁላይ 1990 ያፀደቀውን የሕፃናት መብትና ደኅንነት በሚመለከት የወጣውን የአፍሪካ ቻርተር በሥራ ላይ ማዋል በማስፈለጉ፤
ቻርተሩ በሥራ ላይ የሚውለው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ጸሐፊ 15 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሀገሮችን የቻርተሩ ማፅደቂያ ሰነዶች ከተቀበለበት ወይም የእነዚህ ሀገሮች ስምምነት ከተገኘበት ከ30 ቀን በኋላ እንደሚሆን በቻርተሩ የተገለጸ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 27 ቀን 1994 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•