የአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቻርተር እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 31 ቀን 2016 በአፍሪካ ህብረት መደበኛ ስብሰባ ወቅት ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ፣
ቻርተሩ የመንገድ ደህንነት ደረጃዎችንና ስልቶችን በግልጽ በማስቀመጥ በሀገርና በአህጉር ደረጃ ሊተገበሩ የሚገባቸውን የመንገድ ደህንነት ጉዳዮች በመደንገግ አባል ሀገራት የላቀ የመንገድ ደህንነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ፤
ኢትዮጵያ ይህን ቻርተር መቀበሏ በሀገር ደረጃ ለህዝባችን ደህንነትና ለሀገራችን ኢኮኖሚ ከሚያስገኘው የጎላ ጥቅም በተጨማሪ የሀገራችንን ገጽታ በእጅጉ ከፍ የሚያደርገውና ኢትዮጵያን በዓለም ዓቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ እንድትሆን በማድረግ ረገድ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ ስለታመነበት፤
ይህንኑ ቻርተር የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 5 ኛ ልዩ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥት አንቀጽ 55 (12 ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•