የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሠላም፣ ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አስተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁሉም ደረጃ ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ሀሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር የአመራር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ችግር ፈቺ ምርምር በማካሄድ ሳይንሳዊ የለውጥ ሀሳቦችን በማመንጨት የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ሁለንተናዊ ብልጽግና እና መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ የሚያስችል የአመራር ልህቀት አካዳሚ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የልማትና የመልካም አስተዳደር ፖሊሲዎችን ሥራ ላይ በማዋል ተቋማዊና ሀገራዊ ለውጥ በቀጣይነት ማረጋገጥ የሚችል፤ የአሁንና የመጪውን ጊዜ ፈተናና ለውጥ በመምራት የአፍሪካን ዘላቂ ልማትና ትስስር በማምጣት በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ አመራር ማፍራት የሚችል ተቋም መገንባት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1ሺ97/2ሺ11 አንቀጽ 34 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል።
•