የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት በተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሥር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም በተቋሙ እንዲተገበር ያስተባብራል፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የቅሬታና አስተያየት አቀራረብ ሥርዓት ቀርጾ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ የተገልጋይ እርካታ ደረጃ መለኪያ ሥርዓት ይቀርፃል፣ ይለካል፣ የመልካም ተቋማዊ ባህል ግንባታ ማዕቀፍ ይቀርጻል፣ እንዲተገበር ያስተባብራል፣ ከተቋሙ ተልዕኮ አንጻር የለውጥ መሳሪያዎች ይለያል ፣ይቀርፃል ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፣ የሃብት ማፈላለጊያ ፕሮጀክቶችን መነሻ ሃሳብ ያዘጋጃል ወይም ለሚያዘጋጁ አካላት ድጋፍ ይሰጣል፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ቴክኒካዊ እና የገንዘብ ድጋፍ እድሎችን ያፈላልጋል፣ ይለያል፣ የድጋፍ ጥያቄ ያቀርባል፣ የፍትሕ ሥርዓቱን የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች አተገባበር ዙሪያ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል፣ በስትራቴጅክ ዕቅድ የተለዩ ፕሮጀክቶች ቀረፃና ሀብት ማሰባሰብ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
