በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በሲዳማ በሔራዊ ክልል ማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የቅንጅት መድረክ ተካሄደ

FDRE Ministry of Justice Facilitated a Coordination Forum for Judicial and Justice Sector Bodies Focused on Community-Based Justice Service Delivery in Sidama National Regional State

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በሲዳማ በሔራዊ ክልል ማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የቅንጅት መድረክ የክልሉ ምክር ቤት የሕግ እና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የክልሉ ባህል እና ስፖርት ቢሮ እና ሌሎች አጋር አካላት በተገኙበት በሐዋሳ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና የለውጥ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኖህ ታከለ ባደረጉት ንግግር፤ የፎረሙ ዓላማ በሲዳማ ክልል በተቋቋመው በማህበረሰባዊ ፍትሕ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ውጤታማነት ላይ ትኩረት በማድረግ በሚመለከታቸው የፍትሕ ተቋማት መካከል የቅንጅት ስራና ትብብር እንዲኖር ማበረታታት መሆኑን ገልጸው፤ የባህላዊ ዳኝነቱን ተደራሽ የማድረግ፣ ወጥነት ያለው እንዲሆን በማድረግ የህዝቡን የፍትሕ አመኔታ ለማረጋገጥ፣ ፍትሕን ወደ ማህበረሰቡ ለማስጠጋትና ህብረተሰቡ ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረግ በማሰብ እና ባህላዊ ዳኝነቱን ከዘመናዊ የፍትሕ ስርዓት ጋር በማጣጣም የፍትሕ አሰጣጥ ስርዓትን አርኪ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው ጠለቅ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፣ የተሳታፊ ተቋማት ሚናና ኃላፊነት፣ የህብረተሰቡ የፍትሕ ሂደት ተሳትፎ አስፈላጊነት እንዲሁም የማኅበረሰብ ፍትሕ ማዕከል በሌሎች የክልሉ ዞን እና ወረዳዎች ሊስፋፋ የሚችልበትን ሁኔታ የተመለከቱት ጉዳዩች ይጠቀሱበታል።

መድረኩ ማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን ለማስፋፋት ቀጣይነት ያለው ትብብርና የጋራ ጥረት እንዲደረግ ስምምነት ላይ በመድረስ ተጠናቋል።

የቅንጅት መድረኩ ሂል ኢንስቲዩት እና ዴስቲኒ ኢትዮጵያ ባደረጉት ድጋፍ መካሄዱ ተጠቁሟል።

Tagged Under: access Access to Justice Civil Justice community-based community-based justice Conflict Resolution Coordination democratic destiny ethiopia FDRE federal federal democratic republic of ethiopia (fdre) judicial Justice Justice Sector Reform justice service delivery legal legal pluralism participatory justice pluralism reform republic sector sidama traditional traditional justice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች