የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በቀጣይ 5 አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር የቀጣይ 5 አመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ ቀርቦ የተጠሪ ተቋማቱም ያለፈው አመት ዋና ዋና አፈጻጸም እና የቀጣይ አመታት ትልሞች ቀርበዋል።ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከቅንጅታዊ አሰራር፣ ከዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ እና ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን ማሳደግ አንፃር በቀጣይ 5 አመታት ጠንካራ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠሪ ተቋማት እቅዶቻቸውን ከዚህ አንጻር እንዲከልሱ አቅጣጫ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።