የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከUnited Nations Development Programme እና Hague Institute for Innovation of Law ጋር በመተባበር ለደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሺሺንዳ ሞዴል ባህላዊ ፍርድ ቤት የቢሮ ዕቃዎች እና ለሽማግሌዎች የአቅም ግንባታ የሥልጠና የወጪ ድጋፍ አደረገ።
የሞዴል የባህል ፍርድ ቤቱ ይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃንን ጨምሮ የሺሺንዳ ከተማ ከንቲባ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር በተገኙበት ሰኔ 4/2018 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ወቅት እንደተገለፀው በክልሉ 700 ቀበሌዎች ላይ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን፤ በበጀት ዓመቱ ብቻ 1‚700 በላይ መዛግብቶችን መታየት ችለዋል፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴርም በክልሉ የባህል ፍርድ ቤቶች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የተቋቋሙትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ከአጋር አካላቶቹ ጋር በመሆን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳታውቋል፡፡
በነገው እለትም የድጋፉ አካል የሆነው የባህል ፍርድ ቤት ሽማግሌዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መርሃ-ግብር እንደሚጀምር ተጠቁሟል፡፡